የኢትዮጵያ ድረ-ገጽ
በአፍሪካ ቀንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ ከ120 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ሲሆን በሕዝብ ብዛት በአህጉሩ ሁለተኛዋ አገር ነች። ኢኮኖሚዋ በፍጥነት እያደገ ቢሆንም በዋነኛነት በእርሻ ላይ የተመሰረተ ዝቅተ ኛ ገቢ ያላት ሀገር ሆና ቆይታለች። ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች ያሏት ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የጎሳ ግጭቶችን አስተናግዳለች።
ኢኮኖሚዋ በፍጥነት እያደገ ቢሆንም በዋነኛነት በእርሻ ላይ የተመሰረተ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ሀገር ሆና ቆይታለች። ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች ያሏት ሀገሪቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የጎሳ ጥቃቶች ታይተዋል።

የጌጅ ጥናት አጠቃላይ እይታ
የጌጅ ጥናት አጠቃላይ እይታ
የጌጅ ጥናት በኢትዮጵያ የወጣቶችን ዘርፈ ብዙ አቅም እና ክወጣትነት ወደ ጎልማሳነት ዕድሜ ሲሸጋገሩ የሚያጋጥሟቸውን እድሎችና አደጋዎች እንዴት ከተለያዩ ሁኔታዎች አኳያ ለምሳሌ ከጾታ፣ ከጎሳ፣ ከመኖሪያ አካባቢ፣ ከአካል ጉዳት እና ከጋብቻ ሁኔታ አኳያ እንደሚለያዩ ይዳስሳል። የጌጅ ጥናት በወጣቶች ዙሪያ እየተተገበሩ ያሉ ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች እንዲሁም የእነዚህ ትግበራ በወጣቶች ላይ ያመጣው ለውጥ ምን እንደሚመስል መዳሰስ ላይ ያተኩራል፡፡
ጌጅ በኢትዮጵያ ውስጥ ሶስት የተለያዩ የስራ ዘርፎች ያሉት ሲሆን ሁሉም የረዥም ጊዜና (longitudinal) ቅይጥ (mixed) ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ዋናው የጌጅ የጥናትና ምርምር ፕሮግራም በዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ የኮመንዌልዝ እና ልማት ጽ/ቤት (FCDO) የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄድ ሲሆን ከዘጠኝ ዓመታት በላይ (እ.ኤ.አ. 2016-2024 ዓ.ም.) በገጠር የሚኖሩ ከ10,000 በላይ ታዳጊዎችን በሶስት ክልሎች (አፋር ዞን 5፣ አማራ እና ኦሮሚያ) እና ሶስት ከተሞች (ባቱ፣ ደብረታቦር እና ድሬዳዋ) እየተከታተለ ይገኛል። እንደዚህ ጥናት አካል፣ በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጃገረዶችን የትምህርት፣ የጤና፣ የስነ-ልቦና እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን ለማሻሻል ዓላማ ያለውንና በፓዝፋይንደር ኢንተርናሽናል እና ኬር ኢትዮጵያ የተተገበረውን የአብረናት እንተግብር (Act with Her (AwH)) ፕሮግራም ተጽእኖዎችንም እየገመገምን ነው።
የጌጅ ሁለተኛ ጥናት፣ በኢትዮጵያ የአየርላንድ ኤምባሲ በኩል በአይሪሽ ኤይድ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ በአምስት ዓመታት ውስጥ (እ.ኤ.አ. 2022-2026 ዓ.ም.) በሁለት አርብቶ አደር ክልሎች (አፋር እና ሶማሌ) የሚኖሩ ከ2,000 በላይ ታዳጊዎችን እየተከተለ ይገኛል። የዚህ ጥናት አካል የሆነው የሴት ልጅ ግርዛትን እና የህጻናት ጋብቻን በመቀነስ እንዲሁም የልጃገረዶችን እና ሴቶችን በማህበራዊና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን በማጎልበት ዙሪያ ያተኮረውን በሴቭ ዘ ችልድረን ኢንተርናሽናል የተተገበረውን ፕሮግራም ተፅእኖም እየገመገምን ነው።
እ.ኤ.አ. በ2024 ዓ. ም. የጀመረው የጌጅ ሶስተኛ ጥናት የአየር ንብረት ለውጥና በቅርብ ጊዜ የተከሰተው ግጭት (2020-2022 እኤአ) በአፋር ክልል (ዞን 2) እና ትግራይ ክልል በሚኖሩ ወጣቶች ላይ ያስከተለውን ዘርፈ ብዙ ተጽእኖ ይዳስሳል። ይህ የናሙና ጥናት በግጭት በተጎዱ ማህበረሰቦች ውስጥ የሚኖሩ 2,250 ግለሰቦችን ያቀፈ ነው።
በኢትዮጵያ ጌጅ ከኩዌስት ሪሰርች፣ ስልጠና እና አማካሪ ድርጅት፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአሳይታ መምህራን ኮሌጅ፣ ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከተውጣጡ የፍሪላንስ ተመራማሪዎች ጋር በጥምረት ይሰራል። ጌጅ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋርም የመግባቢያ ስምምነት ያለው ሲሆን ክ“ብሄራዊ ትብብር የህጻናት ጋብቻን እና ግርዛትን ለማስቆም” (National Alliance to End Child Marriage and FGM) ጋርም በቅርበት ይሰራል።
የዋናው የጌጅ ጥናተና ምርምር ፕሮግራም የጊዜ ሰሌዳ
2017-2018
መነሻ መስመር
2019-2020
የ 2 ኛ ዙር ክትትል
2020–2021
የኮቪድ-19 መረጃ መሰብሰቢያ ዙሮች
2020–2021
Round 3 follow-up
2023
የአራተኛው ዙር ክትትል (በቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ የተደረገ)
2024–2025
ዙር 5/መጨረሻ
Timeline for GAGE’s pastoralist research
2022
Baseline
2024
Midline
2026
Endline plans
Timeline for the conflict and climate change study
2024
Baseline
2025–2026
Follow-up
የጥናት ዘዴዎች
ጌጅ በኢትዮጵያ የቅይጥ ጥናትና ምርምር ዘዴዎችንና የተጽዕኖ ግምገማ ንድፍን ይጠቀማል፡፡ የመጠናዊ ዳሰሳ ጥናቶች የታዳጊዎችን ትምህርት፣ ጤና፣ አካላዊ ምሉዕነት፣ ከጥቃት ነጻ መሆን፣ ሥነ ልቦናዊ ደህንነት፣ ድምጽና ዉሳኔ ሰጭነት እና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በሁለት የታዳጊዎች እድሜ እርከን (ከ10-12 አመት እድሜ ያለው ትንንሽ ታዳጊዎች ቡድን እና በመንሻ ጥናት ጊዜ ዕድሜው ክ15–17 የሆነ ትልልቅ የታዳጊዎች ቡድን) መሰረት ይዳስሳል፡፡ ክብካቤ ሰጭዎችም የመጠናዊ ዳሰሳ ጥናቱ አካል ነበሩ። የአይነታዊ ጥናቱ አሳታፊ ምርምርን ጨምሮ የግለሰብና የቡድን ቃለመጠይቆችን (ከእድሜ እና ዐውድ አኳያ በጥንቃቄ የተዘጋጁ መሳሪያዎችን በመጠቀም) ከታዳጊዎች፣ ክብካቤ ሰጭዎችና ከተለያዩ ቁልፍ መረጃ ሰጭዎች ጋር የተካሄደ ሲሆን መምህራንና የጤና አገልግሎት ሰጪዎችን፣ ማህበረሰብ፣ ባህላዊ እና የሃይማኖት መሪዎችን፣ እንዲሁም የፖሊሲና ፕሮግራም ባለሙያዎችን ያካትታል።

ናሙና
በኢትዮጵያ፣ በሦስቱ የስራ ዘርፎች፣ ጌጅ ከ12,000 በላይ ታዳጊዎችን በመጠናዊ ጥናቱና ወደ 1,500 ታዳጊዎችን ደግሞ በአይነታዊ ጥናቱ ክትትል ያደርጋል።
የጌጅ ናሙና በጣም የተገለሉና “ለመድረስ በጣም ከባድ” የሆኑ ማህበረሰብ ክፍሎችን ያካትታል። ይህም ከዋና መንገድ ሩቅ የሆኑ ማህበረሰቦችና ወጣቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ በህጻንነታቸው ያገቡ፣ ትምህርት ቤት የማይማሩትን፣ ህጻናት ስደተኞችንና በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉትን ይጨምራል።

ዋና የጥናቱ ግኝቶች
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ታዳጊ የወደፊት ሕይወታቸውን አስተማማኝ ለማድረግ ከሁሉ የተሻለው መንገድ ትምህርት እንደሆነ ቢረዱም፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነት ውስን ነው፤ የትምህርት ጥራትም ዝቅተኛ ነው። ወጣቶች በጤናቸው፣ በአካላዊ ደህንነታቸው፣ በስነ ልቦናና ማህበራዊ ደህንነታቸው እና በወደፊቱ ኑሯቸው ላይ በርካታ ስጋቶች ያጋጥሟቸዋል። እነዚህ ስጋቶች ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ተደጋጋሚና የከፋ የምግብ ዋስትና እጦት፤ በእድሜና በፆታ ላይ የተመሰረተ በቤት፣ በትምህርት ቤትና በማህበረሰብ ውስጥ ይሚያጋጥም ጥቃት፤ እነዚህን ችግሮዎች ለመፍታት የአገልግሎቶች፣ የድጋፍ እና የፍትህ ተደራሽነት ውስንነት፤ ከፍተኛ የወጣቶች ስራ አጥነት፤ እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሄደው የጎሳ ጥቃት ብዙ ወጣቶችን ፈሪና ተስፋ ቢስ አድርጓቸዋል። የኢትዮጵያ ልጃገረዶችም ላለዕድሜ ጋብቻና ለሴት ልጅ ግርዛት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
የጌጅ ጥናት የታዳጊዎችን የትምህርት ተደራሽነት በማስፋትና በማመቻቸት፤ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር መተዳደሪያ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግ፤ የሥርዓተ-ፆታ ማህበራዊ ልማዶች እንዴት የታዳጊዎችን ሰፊ እድሎች እንደሚያኮስሱና እንደሚገድቡ ግንዛቤ ማስጨበጥን በተመለክተ የማብቃት መርሃ ግብሮችን በመንደፍና እና በቅርቡ ከተከሰተው ግጭት በኋላ የማህበረሰቡን ግንኙነትና መስተጋብር እንደገና ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት በተጠናከረ መንገድ መደገፍ የታዳጊዎችን ህይዎት ለማሻሻል ጉልህ ሚና እንዳለው ይጠቁማል።